አል ሀበሻ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት በዱባይ - የኢትዮጵያ የምግብ

መለያችን ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ጣዕም እና ጣፋጭ ምግቦቻችን ናቸው!

አል ሀበሻ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት በአቡዳቢ - የኢትዮጵያ የምግብ

ተፈጥሯዊ ቃና የኢትዮጵያዊ ጣዕም መገኛ ወደሆነው ቤታችን እንኳን በደህና መጡ !

0
ዓመታት ከእርስዎ ጋር!
0
አካባቢዎች
0
ያገለገሉ ምግቦች

እንኳን በደህና መጡ ወደ አል ሀበሻ ሬስቶራንት

በዱባይ እና በአቡዳቢ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት

እንኳን በደህና መጡ ወደ
አል ሀበሻ ሬስቶራንት

በዱባይ እና በአቡዳቢ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት

ዛሬ ይብሉ እንጂ፣ ለነገ ነገ ያስባሉ!

በ ዩኤኢ ከ20 አመት በላይ ልምድ ያለው አል ሀበሻ ሬስቶራንት በአካባቢው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ሲሆን በመላው ኢሚሬቶች ቅርንጫፎች አሉት። ዓላማችን እርስዎ በቤትዎ ያሉ እስኪመስልዎ ምቾት እንዲሰማዎት እና ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ምግቦችን ማዘጋጀት ሲሆን የምንጠቀማቸው ግብዓቶች በሙሉ አዲስ የተቀጠፉ (ፍሬሽ) ምርቶች ናቸው።

የኢትዮጵያ ምግብ በዓለም ውስጥ ምርጥ ከሚባሉት አንዱ ነው። የኢትዮጵያ የምግብ ሙያ ዋና ዋና ክፍሎች በርበሬ፣ ንጥር-ቅቤ እና እንጀራ ናቸው። እንጀራ የሚዘጋጀው ከጤፍ ሲሆን፣ ጤፍ የሚበቅለው ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። እንጀራ የሚዘጋጀው የጤፍ ዱቄት ተቦክቶ በእርሾ ተብላልቶ ስለሆነ በመጠኑ የመቆምጠጥ ባህሪ ያለው ቢሆንም አስደናቂ የሆነ ገፅታን የተላበሰ ነው።
በተለምዶ አንድ ምግብ የሚያካትተው፣ አነስተኛ የቡና ጠረቤዛ የሚያክል እንጀራ እና ሌሎች የወጥ አይነቶች በላይ ተጨምሮበት ነው፤ ለምሳሌ የበሬ ስጋ ወጥ፣ የበግ ስጋ ወጥ፣ የአትክልት ወይም የምስርም ሆነ የተለያዩ አይነት ወጦች የሚጨመሩበት ይሆናል። ምግቦቻችን የሚያካትቱት በቅመማት ተከሽነው የሚቀርቡ የአትክልት፣ የቅቅል ስጋ፣ ወይም የጥብስ ስጋ፣ ክትፎ የመሳሰሉትን ይሆናል። የኢትዮጵያን ምግቦች ለየት የሚያደርጋቸው የምንጠቀማቸው የቅመማ ቅመም አይነቶች እና ልዩ የአዘገጃጀት ጥበባችን ከአመጣጠናችን ጋር ተዳምረው ልዩ ያደርጓቸዋል።

ከቤተሰብዎ እንዲሁም ከጓደኛዎ ጋር ይምጡና ይዝናኑ። ለእርስዎ ድግስ፣ እኛ ሁሉን ነገር በሚገባ አሰናድተን፣ ልዩ እና የማይረሳ ጊዜን እንዲያሳልፉ እናደርጋለን። እያንዳንዱ እንግዳ ልዩ የሆነ ጊዜን እንዲያሳልፍ፣ በባህላዊ የኢትዮጵያ ምግቦች እና በባህላዊ የጀበና ቡና አፈላል ስነ-ስርዓት የታጀበ ዝግጅት ይኖራቸዋል። የኢትዮጵያን የምግብ ጣዕም በአል ሀበሻ ሬስቶራንት ያጣጥሙ።
AWARD WINNING SUSTAINABLE UAE EATING Abu Dhabi 2021 - Chef Sara Aradi

ሽልማት አሸናፊ

ዘላቂነት ያለው ዩኤኢ መመገብ

አቡ ዳቢ 2021

አዲስ የተቀጠፉ (ፍሬሽ) ግብዓቶች
አዲስ የተቀጠፉ (ፍሬሽ) ግብዓቶች
ለጤና ተስማሚ
ለጤና ተስማሚ
የኢትዮጵያን ወግ የጠበቀ
የኢትዮጵያን ወግ የጠበቀ
ምርጥ ምርጡን ይመገቡ
ምርጥ ምርጡን ይመገቡ

ሼፍ ሳራ አራዲ

በገልፍ ምግብ ላይ እንደታየው
(የዓለም ጣዕም ዝግጅት ላይ)

ሼፍ ሳራ አራዲ
ሪዘርቬሽን

ቦታ ለማስያዝ

ያጋሩ
Share on facebook
Facebook
Share on twitter
Twitter
Share on whatsapp
WhatsApp